የተመድ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢትዮጵያ ለስደተኞች እያደረገች ያለውን መስተንግዶ አደነቁ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዴ ኢትዮጵያ በስደተኞች ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ አድንቀዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከኮሚሽነሩ ጋር ተገናኝተዋል።
በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ የሱዳን ስደተኞችን ሰብአዊነት በተሞላበት መንገድ ተቀብላ በማስተናገዷ አወድሰው፥ ለጋሾች በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሳድጉ ጠይቀዋል።
በአሜሪካ ኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተካፈሉ የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ልዑካን ጋር ስኬታማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።