ስለካንሰር ምን ያህል ያውቃሉ ?
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ካንሰር የተዛቡ ህዋሶች በፍጥነት ሲከፋፈሉና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚሰራጭ የበሽታ ዓይነት ነው፡፡
እነዚህ በፍጥነት የሚያድጉ ሴሎችም እብጠቶችን ሊያስከትሉና የሰውነትን መደበኛ ተግባር ሊያዛቡ የሚችሉ ናቸው፡፡
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ፥ ካንሰር በዓለም ላይ ለሞት ከሚዳርጉ ምክንያቶች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው።
የካንሰር አጋላጭ ምክንያቶችን እና መከላከያ መንገዶችን በማወቅ ራስን ከዚህ በሽታ መጠበቅ እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ኬሚካሎች፡ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል፣ የአየር መበከል (ለውጥ)፣ የተበከለ ምግብና ውሃን መጠቀም፣ ቫይረሶች፣ ባክቴሪያ፣ ጥገኛ ተውሳክ፣ ጨረር እና ሌሎች የካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች በመባል ይጠቀሳሉ፡፡
እንደዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ፥ 33 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ሞት በትምባሆ፣ በአልኮል፣ በከፍተኛ የሰውነት ክብደት፣ የፍራፍሬና የአትክልት ፍጆታ ዝቅተኛነት እና በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለማድረግ የሚከሰቱ ናቸው።
በቤተሰብዎ የካንሰር ታማሚ ካለ (ከነበረ) ወይም ለካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ከሆነ የሕክምና ባለሙያዎችን ምክር መከተል አስፈላጊ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
የካንሰር ማስጠንቀቂያ ምልክቶችን ማወቁ ካንሰር ያለባቸው ሰዎች ምርመራ እና ህክምና እንዲያገኙ ሊረዳቸው ይችላል፡፡
ሆኖም አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ቀደም ብሎ ለመለየት ከባድና እስከ መጨረሻ ደረጃዎች ድረስ ምልክቶች ላያሳዩ እንደሚችሉም ነው የሚነገረው፡፡
እብጠቶች ወይም ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች የተለየ እድገት ሲታይ፣ ክብደት መቀነስ፣ ትኩሳት፣ ድካም፣ ህመም፣ በምሽት ማላብ፣ የምግብ መፈጨት ለውጥ ወይም መስተጓጎል፣ የቆዳ መቀየር እና ሣል ከካንሰር ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የካንሰር ህክምና እንደ ካንሰሩ ዓይነት እና ምን ያህል የላቀ እንደሆነ በመለየት የሚደረግ ሲሆን ፥ ይህም አንዱ ከአንዱ እንዲለያይ ምክንያት ይሆናል፡፡
የመጀመሪያው የህክምና ዓይነትም እንደ የቀዶ ጥገና ወይም ካንሰር የተከሰተበትን የሰውነት ክፍልን ወይም እጢን በመለየት የሚደረግ የጨረር ህክምና ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ ሌሎች የሰውነት ክፍልን ሊጎዱ የሚችሉ ሲሆኑ ፥ ኬሞቴራፒና ሌሎችን ያካተተ የሕክምና ዓይነት ነው፡፡
ሦስተኛውና የመጨረሻው ደግሞ የማስታገሻ እንክብካቤ ነው ፤ ይህም ከካንሰር ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና እክሎች እንደ የመተንፈስ ችግር እና ህመም ማስታገስ ያካትታል።
የካንሰር ተጋላጭነትን የሚያባብሱ ምክንያቶች
– ሲጋራ አማጨስ
– በከፍተኛ መጠን አልኮል መጠጣት
– ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓት
– የታሸጉ እና የተቀነባበሩ ምግቦች እንዲሁም ለስላሳ መጠጦችን ማዘውተር
– ከልክ በላይ ውፍረት
– ምንም አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
– በከፍተኛ ሁኔታ ለፀሐይ እና ለጨረር መጋለጥ
– በተለያየ አጋጣሚ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች
#cancer #health
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!