ሩሲያ የቻይናን የተኩስ አቁም ጥሪ ተቀበለች
አዲሰ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረች ያለውን ተኩስ እንድታቆም ቻይና ያቀረበችላትን ጥሪ ተቀብላለች፡፡
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፥ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆምና ወደ ድርድር ለመመለስ የቻይናን የአቋም መግለጫ አድንቀዋል ተብሏል፡፡
ላቭሮቭ ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር በሞስኮ ተገናኝተው ባደረጉት ንግግር፥ የአቋም መግለጫው የሁሉንም ወገኖች የጸጥታ ችግር ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ገልጿል።
ባለፈው የካቲት ወር ቻይና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለውን ተኩስ በማቆም ድርድር እንድታደርግ የሚጠይቅ የአቋም መግለጫ አውጥታ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ የምዕራባውያን ከፍተኛ ዲፕሎማቶችና ባለሙያዎች የአቋም መግለጫው ምንም አዲስ ነገር የለውም ሲሉ ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ መስጠታቸውም ነው የተገለጸው።
የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት ቻይና እና ሩሲያ ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂካዊ መረጋጋትን የማስጠበቅ እና የዓለም እድገት ላይ ኃላፊነት አለባቸው ሲል መግለጫው ጠቁሟል።
ዋንግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለሚካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ሰኞ ወደ ሞስኮ መጓዛቸውን የዘገበው ዴይሊ ናይጄሪያን ነው።
#China #Russia #Ukrain #ceasefire
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!