Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት የምርጫ 2012 የማራዘም ውሳኔን እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት የምርጫ 2012 የመራዘምን ውሳኔ እንደሚደግፍ አስታወቀ።
 
ጥምረቱ አስቸኳይ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ አካሂዷል።
 
ቀደም ሲል በመቐለ ጉባኤና በሌሎች ስብሰባዎች ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መካሄድ አለበት ብሎ አቋሙን ሲገልፅ መክረሙን ያስታወሰው ጥምረቱ፤ ይህ ውሳኔ ስህተት በመሆኑ የቀረበውን የመፍትሔ ሀሳብ እንደግፋለን ብሏል።
 
ወቅቱ የኮሮና ቫይረስ የዓለምን ሁኔታ በብዙ መልክ እየቀየረ ያለበት መሆኑን የጠቀሰው ጥምረቱ፥ የኢትዮጵያም ነባራዊ ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም ብሏል።
 
በመሆኑም የወቅቱ ቀዳሚ አጀንዳ ኮሮናን መከላከልና የተደቀኑ የሉዓላዊነት ስጋቶችን ማክሸፍ በመሆኑ የምርጫ መረዛም ውሳኔውን እንቀበላለን ብሏል።
 
ከዚህ ውጪ ጥምረቱ ለዜጎች ሁለንተናዊ ጥቅምና ለሀገር ደህንነት ለመታገል የተመሰረተ እንጂ የማንም ቡድን መልዕክት ተቀባዮች አይደለንም ብሏል።
 
የህዳሴ ግድብም በተባለበት የጊዜ ገደብ እንዲከናወንና ህዝቡም ድጋፉን እንዳያቋርጥ ጥምረቱ ጠይቋል።
 
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት የመጀመሪያ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ያደረገ ሲሆን፥ ይፋዊ ቢሮውን በከተማዋ መክፈቱን እስታውቋል።
 
 
በሀይለሚካኤል ዴቢሳ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.