Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኅዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ተሰሚነት በቀጣናው እንደሚያሳድግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ የሀገሪቷን ምጣኔ ሐብታዊ እና ማሕበራዊ ዐቅም ከማሳደጉ ባሻገር በፖለቲካው ዘርፍ ተሰሚ እንድትሆን ያደርጋታል ሲሉ የቀድሞው የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ተናገሩ፡፡

4ኛው ዙር ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሙሌት ይዞ የመጣውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም በተመለከተ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ነበራቸው፡፡

በኢትዮጵያ የዘርፉ ምሁር የሆኑት ፈቅ አሕመድ ነጋሽ የሚመነጨው ውሃ ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ ከሀገራት ጋር ለመተባበር ፣ ለመደራደር ብሎም ውሳኔ ላይ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ከፍተኛ አቅም እንደሚፈጥር አንስተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሥራ መጀመር የሀገሪቷን ምጣኔ ሐብት በማሳደግ በኩል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋልም ነው ያሉት፡፡

ለአብነትም ሀገሪቷ በቂ የኃይል አቅርቦት ስለሚኖራት የንግዱ እና ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንደሚነቃቃ ጠቅሰው፥ ከማሕበራዊ ጥቅሙ አንፃርም አሁን ላይ በቂ የኃይል አቅርቦት ባለማግኘታቸው አገልግሎት መስጠት የማይችሉ የጤና ማዕከላት ችግር እንደሚቀረፍም ያስረዳሉ።

በተጨማሪም በኤሌክትሪክ ውሃ ስቦ ንፁሕ የመጠጥ ውሃ ለማውጣት እና ለማዳረስ እንዲሁም በሀገሪቷ የማታ ትምህርት ለማዳረስ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር ገልጸዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍም ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ለመስኖ ልማት በቂ የኃይል አቅርቦት ተደራሽ በማድረግ ረገድ ሁኔታዎችን እንደሚያቃልልም ነው ፈቅ አሕመድ ነጋሽ የሚያስረዱት፡፡

ከፍጆታ ባለፈ የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭቶ መሸጥ በሁለተኛነት የሚታይ ጉዳይ መሆኑንም ነው ያነሱት የቀድሞው የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ፡፡

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.