Fana: At a Speed of Life!

ቡሩንዲ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ቡሩንዲ የአለም ጤና ድርጅት ተወካይ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር የአለም ጤና ድርጅት ተወካይን ጨምሮ ሶስት ባለሙያዎች ሃገሪቱን በ48 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውሳኔውን ምክንያት ከመግለጽ ተቆጥቧል።

የቡሩንዲ መንግስት የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ለምርጫ እየተዘጋጀ መሆኑ ጠንካራ ትችት አምጥቶበታል።

ዓለም አቀፍ የቀውስ ቡድን ባወጣው መግለጫ የብሩንዲ መንግሥት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሚወጡ መረጃዎችን እየተቀበለ አይደለም ሲል ተችቷል።

በአገሪቱ እስካሁን 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.