Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 3 ሺህ 580 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 3 ሺህ 580 የላብራቶሪ ምርመራ 9 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 272 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው እለት ባወጡት ሪፖርት አመላክተዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ እድሜያቸው ከ17 እስከ 66 ዓመት የሆኑ 5 ወንዶች እና 4 ሴቶች መሆናቸውን ዶክተር ሊያ አስታውቅዋል።

ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ውስጥ 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፥ 4 ሰዎች ደግሞ ሶማሌ ክልል (ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ) የሚገኙ ናቸው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

3 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፥ ቀሪዎቹ 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው መሆኑንም ዶክተር ገልፀዋል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ45 ሺህ 278 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 272 ደርሷል።

አሁን ላይ 157 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፥ እስካሁንም 108 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፤ የ5 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው ጃፓን መመለሳቸው ይታወሳል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.