Fana: At a Speed of Life!

ለህዳሴ ግድቡ ከ500 ሚሊየን እስከ 700 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ ዓላማ ያለው ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ለአንድ ወር የሚቆይ የሕዳሴ ግድብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ አስጀምሯል፡፡

የገንዘብ ማሰባሰቢያ ንቅናቄው “ግድቤን ለማጠናቀቅ ቃሌን አድሳለሁ”በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተጀመረው፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍቅርተ ታምር እንደገለጹት÷ በንቅናቄው ከ500 ሚሊየን እስከ 700 ሚሊየን ብር ለማሳባሰብ ታቅዷል፡፡

እቅዱን ለማሳካትም ከልማት ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በሀገር ውስጥ እና በውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ለሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.