ዘለንስኪ ተመድ ሩሲያ ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣኗን እንዲያነሳ ጠየቁ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሩሲያን ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣን እንዲያነሳ ጠይቀዋል፡፡
በተመድ 78ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ፕሬዚዳንቱ ሩሲያ በሀገራቸው ላይ የፈጸመችው ድርጊት ድምጽን በድምጽ የመሻር ስልጣኗል የሚያስከለክላት እንደሆነ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፖላንድ ለዩክሬን የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆሟን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዎስ ሞራቪኪ አስታውቀዋል።
ፖላንድ ለዩክሬን የምታደርገውን ድጋፍ በማቋረጥ የራሷ ደህንነት ላይ ትኩረት እንደምታደርግ ጠቅሰው፤ ውሳኔው ሀገሪቱ በዩክሬን የእህል ምርቶች ላይ በጣለችው እገዳ የተነሳውን ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።
በዚህም የሀገሪቱ መንግስት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ወደ ዩክሬን ማጓጓዙን እንደሚያቆም የገለጹት ሞራቪኪ÷ ጉዳዩም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት አጉልቶ እንደሚያሳይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ፖላንድ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ዩክሬናውያን ስደተኞችን ከመቀበል ጀምሮ ወታደራዊ ድጋፍ ስታደርግ እንደነበር ይታወቃል፡፡