Fana: At a Speed of Life!

አዘርባጃን በናጎርኖ ኳራባግ ለተገደሉ የሩሲያ ሰላም አስከባሪዎች ይቅርታ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዘርባጃን በናጎርኖ ኳራባግ ለተገደሉ የሩሲያ ሰላም አስከባሪዎች ይቅርታ መጠየቋን ክሬምሊን አስታውቋል፡፡

የአዘርባጃን ፕሬዚደንት ኢልሃም ኤሊየቭ ÷ ሀገራቸው በወሰደችው የአፀፋ ወታደራዊ ርምጃ በተገደሉ የሩሲያ ሰላም አስከባሪዎች ይቅርታ ጠይቀው በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ለፕሬዚዳንት ፑቲን በስልክ አሳውቀዋል ነው የተባለው፡፡

በዚህም ፕሬዚዳንቱ በሩሲያ ሰላም አስከባሪዎች ሞት ማዘናቸውንና ለተገደሉት ወታደሮች ቤተሰብ ካሳ መስጠታቸውን ክሬምሊን ገልጿል።

አዘርባጃን በናጎርኖ ኳራባግ ድንበር የይገባኛል ጥያቄ  ከአርሜኒያ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ወታደራዊ አፀፋ እየሰጠች በነበረችበት ወቅት የሩሲያ ሰላም አስካባሪ ሀይሎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር መግለጫ÷ የሩሲያ የሰላም አስከባሪዎች ግጭት በተፈጠረበት የናጎርኖ ኳራባግ ክልል በታዛቢነት ሲንቀሳቀሱ ተሸከርካሪያቸው ላይ በመተኮሱ ሁሉም ሰላም አስከባሪዎች ሞተዋል፡፡

ናጎርኖ ኳራባግ ከሶቭየት ህብረት ውድቅት በፊት ከአዘርባጃን በመገንጠል ራስ ገዝ ሆኖ የቆየ ክልል ሲሆን አርሜኒያ አካባቢው ሙሉ በሙሉ ከአዘርባጃን አስተዳደር እንዲወጣ ፖለቲካዊ ግፊት ስታደርግ ቆይታለች ተብሏል፡፡

አዘርባጃን በበኩሏ በአካባቢው የይገባኛል ጥያቄ ስታቀርብ የቆየች ሲሆን አርሜኒያ በአካባቢው የምታደርገውን ፀብ አጫሪ እንቅስቃሴ በመቃወም ወታደራዊ ምለሽ ስትስጥ መቆየቷ ተገልጿል፡፡

ባለፈው ዓመት 100 በላይ ወታደሮችን ከገደለው ግጭት በኋላ በሞስኮ አሸማጋይነት በአካባቢው ሰላም ሰፍኖ እንደነበር አር ቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.