Fana: At a Speed of Life!

ዲሞክራቲክ ኮንጎ የተመድ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከግዛቷ እንዲወጣ ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰላም አስከባሪ ሃይል ከግዛቷ በፍጥነት እንዲወጣ ጥሪ አቅርባለች፡፡

በተመድ 78ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሺሴኬዲ÷ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛቷን የምትቆጣጠርበትና ውስጣዊ ሰላሟን ለመጠበቅ ዋነኛ ተዋናይ የምትሆነበት ጊዜ ላይ ደርሳለች ብለዋል፡፡

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙ ከ15 ሺህ በላይ የሰላም አስከባሪ ሀይሎች በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ አማፂያንና ታጣቂ ቡድኖችን ማስቆም አልቻሉም፣ ንፁሀን ዜጎችንም ከጥቃት መከላከል አልተቻለም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል የሚንቀሳቀሱ አማፂያንን ለመከላከል የተመድ ሰላም አስከባሪ ሀይል ለ25 ዓመታት በሀገሪቱ ተሰማርቶ ቆቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2020 የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኙ ሰላም አስከባሪዎችን ለማስወጣት የውሳኔ ሃሳብ ቢያቀርብም አሜሪካ አለመስማማቷን ተከትሎ ወታደሮቹ እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡

ይህን ተከትሎም የሰላም አስከባሪዎችን የጊዜ መራዘም በመቃወም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በርካታ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በወታደሮችና በዜጎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ዘ ኔሽን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.