ጤናማ እንቅልፍ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንቅልፍ እንደምግብ እና ውሃ ሁሉ ለአንድ ሰው ጤና የማይተካ ሚና እንዳለው ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ጤናማ እንቅልፍ ለአካል፣ ለስነልቦና ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ከመሆኑ አንጻር ቀንን የመወሰን አቅም አለውና በቂ እረፍት በማድረግ ጤናን መጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
እንቅልፍ ወሳኝ የሚባልን የሰውነት ተግባርን አስጠብቆ ይቆያል ፤ ኃይልን ወደነበረበት በመመለስ በጥንካሬ እንዲውሉ ያደርጋል ፤ የጡንቻ ሕብረ ሕዋስ ይጠግናል እንዲሁም አእምሮ አዲስ መረጃዎችን በአዲስ መንፈስ እንዲያስስ ይረዳል ተብሏል፡፡
በአንጻሩ ሰውነትዎ በቂ እረፍት ባለማግኘቱ ትኩረት ማድረግ፣ ራስን መቆጣጠር እንዲሁም በአግባቡ ማሰብ እንዳይችሉ ያደርጋል፡፡
ይህም የየዕለት ተግባራትን በሥራም ሆነ በቤት ላለመከወን እንቅፋት በመሆን ቀንዎ በድብርትና በብስጭት እንዲሁም ትኩረት ካለመስጠት ጋር ተያይዞ ለሚመጡ ችግሮች ያጋልጣል፡፡
ከጤና ጋር ተያይዞም እንቅልፍ ማጣት እንደ የስኳር በሽታ፣ የልብና የደም ሥር ህመም፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ድብርት ለመሳሰሉት ከባድ የጤና እክሎች የመጋለጥ እድልን እንደሚጨምርም ነው የተገለጸው፡፡
ምን ያሕል ሰዓት ነው በቂ እንቅልፍ ለሚለው ጥያቄ እንደእድሜዎት ይለያያል፡፡
ከሥድስት እስከ 13 ዓመት ለሚሆኑ ከዘጠኝ እስከ 11 ሰዓት ፣ ከ14 እስከ 17 ከ8 እስከ 10 ሰዓት፣ ከ18 እስከ 64 ላሉ ከ7 እስከ 9 ሰዓት እንዲሁም ከ64 ዓመት በላይ ለሆኑ ከሰባት እስከ ሥምንት ሰዓት እረፍት ማድረግ አለብዎ፡፡
ሆኖም ከዚህ በላይ ዘረ – መልዎ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚተኑ ሊወስን እንደሚችልም ኽልዝላይን ባሰፈረው መረጃ ጠቅሷል፡፡
በቂ እንቅልፍ እንዲኖር ምን ማድረግ (አለማድረግ) ይገባል?
– መደበኛ የመኝታ ጊዜ ይኑርዎ
– ካፌን ያሉባቸውን ምግቦች ወይም መጠጦች(ሻይ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ ቡና እና ቼኮሌት) ያስወግዱ
– ስልክዎን ጨምሮ የተለያዩ የኤሎክሮኒክስ አገልግሎቶችን ከርስዎ ያርቁ፡- ይህም ከመተኛትዎ አንድ ሰዓት በፊት ነው፡፡
– አልኮል አይውሰዱ፡፡
#health #sleep
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!