Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ ለኮቪድ-19 የመከላከያ 800 ሺህ ብር የሚገመት የቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ግንቦት6፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍርካ አገራት የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) ለጤና ሚኒስቴር 800 ሺ ብር የሚገመት ለኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
 
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ድጋፉም በድንበር ፣ በተፈናቃዮቸ አከባቢና በስደተኞች ካምፕ የሚሰራውን የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ተግባርን ለማገዝ የሚዉል መሆኑንተናግረዋል።
 
በኢትዮጵያ የኢጋድ የጤናና ማህበራዊ ጉዳይ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ግሩም ሀይሉ በበኩላቸው ÷ድጋፉ የእጅ ጓንት፤ የፊት መሸፈኛ፤ የእጅ ንፅህና መጠበቅያና ሌሎችም ቁሳቁሶች ይገኙበታል ብለዋል።
 
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረገው ድጋፉ የሚቀጥል መሆኑንዶክተር ግሩም መግለጻቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.