Fana: At a Speed of Life!

ፒሮላ የተሰኘ አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፒሮላ የተባለ አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ በኒውዝላንድ ቆሻሻ ውሃ ውስጥ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

ቫይረሱ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥርጭቱን ሳይጀምር አልቀረም ተብሏል፡፡

የዘርፉ አጥኚዎች ቢኤ.2.86 የሚል መጠሪያ የተሰጠውን የኦሚክሮን ንዑስ ዝርያ ሥርጭት ካለፈው ነኀሤ ወር ጀምሮ በንቃት ሲከታተሉ ነበር ተብሏል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱ ሥርጭት በመጀመሪያ ዴንማርክ እና እስራዔል ላይ መገኘቱን ጠቅሶ ቀስ በቀስ በመላው ዓለም እየተሰራጨ ነው ብሏል።

ቫይረሱ ከቀድሞው ይልቅ የከፋ ወይም ከፍተኛ የመተላለፍ ዐቅም ያለው እንደሆነ የሚጠቁሙ ምልክቶች አለመገኘታቸውን ሺንዋ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.