Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፓኪስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ በፓርላማ ትብብር ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር እና በተለያዩ መስኮች ጠንካራ ትብብርን ለማጎልበት በፓርላማ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
ውይይቱ የተካሄደው በፓኪስታን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር አብዱላ እና ከፓኪስታን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር መሐመድ ሳዲቅ ሳንጃራኒ በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይታቸውም የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ትብብር ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
አምባሳደር ጀማል በከር መሀመድ የሀገራቱን ኢኮኖሚያዊና ቢዝነስ ትስስሮሽ በማጠናከር የንግድ ልውውጣቸውን ማሳደግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
አያይዘውም ሊቀ መንበሩ የሰው ዘር መገኛ እና የአፍሪካ አህጉር መግቢያ የሆነችውን ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ መጋበዛቸው ተገልጿል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.