Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገለጹ።

አቶ ደመቀ በሴቶች የፋይናንስ አካቶነት ላይ ባተኮረውና ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው መድረክ ላይ ሳትፈዋል።

በዚህ ወቅትም የ2030 ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሴቶችን በሁሉም የህብረተሰብ ህይወት ውስጥ ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አያይዘውም ትክክለኛ የሴቶች ውክልና የሀገሪቱን ሁለንተናዊ አቅም ለመጠቀም ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ መንግስትም የፋይናንስ አካታችነት በመተግበር ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑንም አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.