የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎቸን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሕብረት በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎቸን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከአውሮፓ ሕብረት ፕሮጀክት ጋር ያከናወናቸውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች ገምግሟል፡፡
በግምገማ መድረኩ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን ÷ ከአደጋ ምላሽ ስራዎች በተጨማሪ የአደጋ ስጋትን ታሳቢ ያደረጉ የልማት ስራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
በተለያዩ ክልሎች የሚተገበሩ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ፕሮጀክቶችን ሁሉም ክልሎች የራሳቸው አድርገው መደገፍ እንደሚገባቻውም አስገንዝበዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረትፕሮጀክት ሃላፊ አቶ አያጣም ፈንታሁን በበኩላቸው÷ ሕብረቱ በኢትዮጵያ የሚተገብራቸው ፕሮጀክቶች የዜጎችን ህይወት እየለወጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የአውሮፓ ሕብረት የሚያከናውናቸውን የአደጋ ቅነሳ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመድረኩ የአውሮፓ ሕብረት በአደጋ ቅነሳ ዙሪያ ያከናወናቸው ተግባራት፣ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ምክክር መደረጉን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡