Fana: At a Speed of Life!

ግብርናን በማዘመን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አበረታች ናቸው- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርናን በማዘመን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የአቡካዶ፣ አኩሪ አተር፣ በቆሎ እና ቦሎቄ ክላስተር ማሳን ጎብኝተዋል።

አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት÷ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ከሚገኙት ዘርፎች መካከል ግብርና ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል።

በዚህም በየአካባቢው የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና የሰው ሃይልን በማስተባበር ኢኮኖሚውን ለማጎልበት ግብርናን የማዘመን ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በተለይ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚችሉና ከውጭ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት የተከናወነው ስራ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በግብርናው ዘርፍ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እየተከናወኑ መሻሻል እየታየባቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዘርፉ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መሻሻሎችን እያሳየና ተጠቃሚነትንም እያጎለበተ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.