Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን የ”ዮ ማስቀላ” የዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)  የ”ዮ ማስቀላ” በዓል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ፡፡

በዓሉን አስመልክቶም “ባህላችን ለዘላቂ ሠላምና ልማት” በሚል መሪ ሃሳብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚዬም ተካሂዷል፡፡

በሲምፖዚዬሙ በጋሞ፣ ዘይሴና ጊዲቾ ብሔረሰቦች ቋንቋ የታተሙ የ1ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍት እና “የጋሞ ዞን ባህል ተምሳሌት” የተሰኘ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡

የ”ዮ ማስቃላ” በዓል በዓመት ከመስከረም እስከ ታህሳስ “ዮ ማስቃላ ፣ ጉጌ ማስቃላ እና የጮዬ ማስቃላ በሚል ሦስት ጊዜ እንደሚከበር የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ  ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.