Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎች ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ያሰናዳው 3ኛው ዓለም አቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ጉባዔው ዓለም አቀፍ የመድኃኒት አቅራቢዎችና አምራቾች በሀገር ውስጥ እንዲያመርቱ የኢንቨስትመንት ዕድል ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አምራችና አቅራቢ የሌላቸው መድኃኒቶችን እንዲሁም የሕክምና ግብዓቶች ተጨማሪ አቅራቢዎች እንዲኖራቸው ያስችላል ነው የተባለው፡፡

እንዲሁም በመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ የሚታዩ ችግሮችን በውይይት ለመፍታትና አምራቾች ምርታቸውን በሀገር ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ለማድረግ ስለመታሰቡም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት 83 በመቶ የሚሆነውን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች አቅርቦት እንደሚሸፍንም በመድረኩ ተነስቷል።

በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተጠቃሚነት በመርኅ ላይ የተመሰረተ በማድረግ የሀገር ውስጥ እምቅ አቅምን ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት፣ መድኃኒት አቅራቢዎችና አከፋፋዮች እንዲሁም አምራቾች በመድረኩ ላይ በአካል የተገኙ ሲሆን÷ በመላው ዓለም የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ደግሞ በበይነ-መረብ እየተሳተፉ ነው፡፡

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.