ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሄ ላይ ለመድረስ አበክራ ትሰራለች – አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የጋራ መፍትሄ ላይ ለመድረስ ኢትዮጵያ በቀና መንፈስ አበክራ ትሰራለች ሲሉ የኢትዮጵያ ወገን ተደራዳሪዎች ልዑካን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ።
አምባሳደር ስለሺ (ዶ/ር) በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ማምሻውን መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በሀገራቱ መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለማጥበብ ድርድርና የሃሳብ ልውውጥ መካሄዱን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሄ ላይ ለመድረስ በቀና መንፈስ አበክራ ትሰራለች ብለዋል።
ሁለተኛው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ደንቦችና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ትናንት በአዲስ አበባ መጀመሩ ይታወሳል።