Fana: At a Speed of Life!

የአብሽ የጤና ጥቅሞች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አብሽ የተለያዩ የጤና በረከቶች ያሉትና ለመድሃኒትነት የሚያገለግል ዕጽዋት ነው፡፡

በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት አብሽ የቆዳ በሽታዎችንና ሌሎች በርካታ በሽታዎችን ለማከም በአማራጭ መድሃኒትነት ጥቅም ላይ እንደዋለ ይነገራል፡፡

የተለመደ የቤት ውስጥ ቅመም ሲሆን፥ ከዚህ ባሻገርም እንደ ሳሙና እና ሻምፑ ባሉ ብዙ ምርቶች ውስጥ በመካተት ጥቅም እንደሚሰጥም ነው የሚገለጸው፡፡

በውስጡ የተለያዩ ማዕድናትን ያካተተው አብሽ ፋይበር፣ ብረትና ማንጋኒዝ የያዘ ነው፡፡

በዕጽዋቱ ላይ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚሉት፤ አብሽ የጡት ወተት ምርትን ይጨምራል፤ ከዚህም ባለፈ አዲስ የሚወለዱ ሕፃናት ክብደታቸው ጤናማ በሆነ መንገድ እንዲጨምር ያደርጋል።

አብሽ የወንድ የዘር ፍሬን (ቴስቶስትሮን) የሚጨምር እንደሆነም ነው በዘርፉ የተጠኑ ጥናቶች የሚያመላክቱት፡፡

ከዚህ ባለፈ አብሽ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመቆጣጠርና በዓይነት-2 የስኳር በሽታ ሕክምና ላይ ሚናው የላቀ ቢሆንም የዓይነት-2 የስኳር በሽታ ታማሚዎች አብሽ ከመውሰዳቸው በፊት ሀኪም ሊያማክሩ ይገባል፡፡

የመመገብ ፍላጎትም በመቀነስ አላስፈላጊ ስብን በማስወገድ የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል፤ ቃርን ይከላከላል፤ ይቀንሳል፡፡

ሆኖም የሚወስዱትን አብሽ መመጠን ያስፈልጋል። የአመጋገብ ስርዓት መዛባት ውስጥ ላሉና ክብደት መጨመር ለሚፈልጉ ሰዎች የሚመከር እንዳልሆነ ኽልዝላይን በዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.