Fana: At a Speed of Life!

በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የሚገነባው የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በበጀት ዓመቱ ይጠናቀቃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት በበጀት ዓመቱ እንደሚጠናቀቅ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ባሌ ዞን ደሎመናና ሃረና ቡሉቅ ወረዳዎች ውስጥ የሚተገብረው የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 11 ሺህ 40 ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።
በታህሳስ 2012 በጀት ዓመት ግንባታው የተጀመረው ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ22 ሺህ በላይ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ 3 ሜትር ከፍታና 50 ሜትር ርዝመት ያለው የወንዝ መቀልበሻና 30 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መጋቢ የውሃ ቦይ ግንባታ እንዲሁም ሌሌች የተለያየ መጠን ያላቸው የመስኖ መሰረተ ልማት እንደሚኖረው ተገልጿል።
በ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው ፕሮጀክት በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሚሆኑ አርሶ አደሮች በዓመት ከ3 ጊዜ በላይ ምርት ማምረት የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
የሲሚንቶና የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንዲሁም አልፎ አልፎ መቆራረጥ እና በስራ ለይ ያሉ የንዑስ ተቋራጮች አቅም ማነስ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ተግዳሮቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።
ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ እንደሆነም መረጃው ጠቁሟል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.