ስፓርት

በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍጻሜ ደረሱ

By Mikias Ayele

September 25, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡

በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተጫወተው ሃድያ ሆሳዕና በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።

በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በመለያ ምት 5 ለ 4 በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚ መሆን ችሏል፡፡

በ17ኛ የአዲስ አበባ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ የተሸነፉት ኢትዮጵያ መድን እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደረጃ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡