Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከግብርና ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የግብርና ሚኒስቴር አመራሮች በመስኖ ስንዴ ልማት፣ በእንስሳት ልማት፣ በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም እና  በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተከናወኑ ተግበራትን አስመልክተው ገለጻ አድርገዋል።

በዚህ ቅትም የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ  አጠናክሮ እንደሚቀጥል የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም የተጀመሩ የግብርና ልማት ስራዎች እንዲጠናቀቁ  ባንኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለጹን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.