Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ካዛኪስታን ወዳጅነትን በይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ካዛኪስታን የፓርላማ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነትን በይበልጥ ለማጠናከር ያለመ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮ- ካዛኪስታን የፓርላማ ወዳጅነት ቡድን በኢትዮጵያ የካዛኪስታን አምባሳደር ጋር መክሯል፡፡

የቡድኑ ሰብሳቢ ቤተልሔም ላቀው (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳሉት÷ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት በትምህርት፣ በቱሪዝም ፣ በፓርላማ አሠራርና ዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

የካዛኪስታን አምባሳደር በበኩላቸው÷ የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በተለይም በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ላይ በትብብር መሥራትና ልምዶችን መለዋወጥ እንደሚገባም ነው ያነሱት፡፡

የኢትዮ-ካዛኪስታን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በፈረንጆቹ መስከረም 5 ቀን 2011 መመስረቱን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.