Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉዳይን አፍሪካ በግንባር ቀደምትነት መምራት እንዳለባት ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉዳይን በመምራት ረገድ አፍሪካ ግንባር ቀደም መሆን አለባት ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የመሠረተ ልማትና ኢነርጂ ኮሚሽነር አቡ-ዘይድ አማኒ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ኮሚሽነሯ ከCOP28 በፊት በተካሄደው 1ዲግሪ ሴንቲግሬድ የኢነርጂ ሽግግር ላይ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ርምጃ ላይ ያላትን መሪነት በማጉላት ጠንካራ አስተያየት ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሯ በንግግራቸው አፍሪካን በኢንቨስትመንትና በፕሮጀክት ትግበራ መደገፍ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ግቦች መሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ያልተመጣጠነ ተፅዕኖ ቢኖራትም በዓለም ከሚለቀቀው በካይ ጋዝ ውስጥ ጥቂቱን ብቻ እንደምታዋጣ ገልጸዋል።
አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረትና የኢነርጂ ጉዳዮችን ለመፍታት ዋና ማዕከል መሆኗን የጠቀሱት ኮሚሽነሯ፤ ለአፍሪካ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ብቻ በቂ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
የፕሮጀክት አተገባበርን ማፋጠን፣ ጥብቅ የጊዜ ገደቦችን ማውጣትና የአየር ንብረት ለውጥን አጣዳፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በፍጥነት መንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በአፍሪካ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በርካታ ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ለስራ ዕድል ፈጠራና ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት አስተዋፅኦ ለማበርከት ሙሉ የእሴት ሰንሰለቶችን ማዘጋጀት እሴትን ለመጨመር አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የCOP28 ጉባኤም በግብፅ ፕሬዚዳንትነት በተካሄደው COP27 ጉባኤ የተጀመሩትን አፍሪካን የተመለከቱ ተጨባጭ ጉዳዮች እንደሚረዳ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.