Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ልትገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ ከፈረንጆቹ 2027 ጀምሮ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ልትጀምር ማቀዷ ተገለጸ፡፡

ዕቅዱ የሀገሪቷ የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ከዓየር ብክለት ነጻ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት በማስፈለጉ ነው ተብሏል፡፡

የሀገሪቷ የኒውክሌር ኃይል እና ኢነርጂ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ጀስተስ ዋቡያቦ እንደተናገሩት ÷ ኤጀንሲው ግናባታውን ሊጀምር ያቀደው በኪሊፊ ወይም በኩዋሌ ነው፡፡

ኬንያ ከሁለቱ በአንዱ አካባቢ የኒውክሌር ማበልጸጊያ ግንባታውን ለመጀመር ያለመችው በፈረንጆቹ 2021 ላይ የዓለምአቀፉን የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ፈቃድ ጠይቃ ይሁንታን በማግኘቷ መሆኑን ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል፡፡

ኬንያ ግንባታውን ለማካሄድ ዓለም አቀፍ ጨረታዎችን እንደምታወጣም ተነግሯል፡፡

የኃይል ማመንጫው 1 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመንጭም ዘገባው አመላክቷል።

ኬንያ አብዛኛው የኤሌክትሪክ ኃይሏን ከእንፋሎት ኃይል የምታገኝ ሲሆን፥ የአሁኑ ፕሮጀክት ግንባታም ይህን ድርሻ ለማመጣጠን ያለመ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.