Fana: At a Speed of Life!

በቀዝቃዛ አየር የሚቀሰቀሰውን አስም እንዴት ማከም ይቻላል?

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዝቃዛ አየር ወቅት አስም የሚባባስበት ሁኔታ ከፍተኛ እንደሆነ የሕክምና ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡

በቀዝቃዛ አየር አስም ያለባቸው ሰዎች ለመተንፈስ የሚፈተኑት ተለምዷዊ ተግባራቸውን እንዳይከውኑ እንቅፋት በመሆንም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴን ስለሚያስተጓጉል ነው፡፡

ለአስም ህሙማን የማይመከረው ያለጥንቃቄ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ማሳልና መሰል የመተንፈሻ ችግሮች እንዲገጥመን መነሻ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ምልክቶቹም ለመተንፈስ መቸገር፣ ማሳል፣ በሚተነፍሱበት ጊዜ ያልተለመደ ድምጽ ማውጣት፣ በደረትዎ አካባቢ ሕመምና የሚያስጨንቅ ስሜት ናቸው፡፡

ቀዝቃዛ አየር እና አስምን ምን አገናኛቸው?

አስም የአየር መተላለፊያ ቱቦዎችን በማሳበጥ ለመተንፈሻ ችግር እንዲጋለጡ የሚያደርግ ሲሆን፥ የአየር መተላለፊያ ቱቦዎች ማበጥም በበቂ ሁኔታ አየር መሳብ እና ማስወጣት አዳጋች እንዲሆን ያደርጋሉ።

ለዚያም ነው አስም ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለመተንፈስ የሚቸገሩት ይላል ኽልዝላይን በዘገባው፡፡

ብዙ ጥናቶች እንደሚሉት በቀዝቃዛ የአየር ንብረት ወቅት አስም ያለባቸው ሰዎች ለመተንፈስ ችግር ስለሚጋለጡ የሕክምና ድጋፍ ይበልጥ የሚሹበት ጊዜ ነው፡፡

አስም ያለባቸው ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከማድረጋቸው በፊት፡-

– ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ወደውስጥ መተንፈስ የምታስችለውን መሳሪያ መጠቀም የመተንፈሻ ቱቦዎች በቀላሉ አየር ማስገባትና ማስወጣት እንዲችሉ ለማድረግ ያስችላል፣
– ወደውስጥ እንዲተነፍሱ የምታግዘውን መሳሪያ መያዝዎን አይርሱ፡፡ ምክንያቱም ምናልባት እንኳን አስምዎ ቢነሳ ለመተንፈስ እንዳይቸገሩ ይረዳዎታል፣
– ወደዋናው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከመግባትዎ በፊት ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ማሟሟቅ፣
– ፎጣ ወይንም ማስክ ማድረግ።

አስም ያለባቸው ሰዎች ምን አይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ አለባቸው?

በቀዝቃዛ አየር ወቅት አስም ለሚያስቸግራቸው ሰዎች ከሁሉም በላይ ከሀኪም ጋር መምከር ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ መውሰድ ያለብዎ መድሃኒት ካለም በአግባቡ መውሰድ፡፡

– ከዚህ ባለፈም በክረምት ወቅት ተጨማሪ ፈሳሽ መጠጣትዎን ይቀጥሉ፡፡ ይሕም በሳንባዎ ውስጥ ያለውን ፈሳሽ ሰውነትዎ በቀላሉ እንዲያስወግድ ያደርገዋል።
– ራስዎን ለበሽታ ከተጋለጡ ሰዎች ያርቁ፣
– ቀደም ብለው ጉንፋን እንዳይዝዎ መከላያ ክትባት ይውሰዱ፣
– የቤት ውስጥ ብናኞችን፣ አቧራና ቆሻሻን ያስወግዱ፣
– በየሳምንቱ አንሶላዎንና ብርድ ልብስዎን በሙቅ ውሃ ውስጥ ይጠቡ፣
– ሲጋራ አያጭሱ፤ ከሚያጨሱ ሰዎችም ይራቁ፣
– ጠንካራ ሽቶዎችን አይጠቀሙ፤ ከሚጠቀሙ ሰዎችም ይራቁ፣
– እንቅስቃሴዎን ይቀንሱ፣
– ጭንቀትን ያስወግዱ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.