በኢራቅ በሰርግ ሥነ ስርዓት በእሳት አደጋ የ100 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ኢራቅ በሰርግ ሥነ ስርአት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 100 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ።
በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ 150 ሰዎች መቁሰላቸውንም ነው ቢቢሲ በዘገባው ያመላከተው።
የእሳት አደጋው መንስኤ በሰርጉ ላይ የተተኮሰ ርችት ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው።
ባለስልጣናት በበኩላቸው በቦታው ላይ ያሉ ተቀጣጣይ ነገሮች እሳቱን አባብሰውት ሊሆን ይችላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሙሽሮቹም ከተጎጂዎች መካከል እንደሚገኙ የነነዌ የጤና ዳይሬክቶሬት ምክትል ኃላፊ ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራቅ ቀይ ጨረቃ ማህበር በቃጠሎው ከ450 በላይ ሰዎች የሞት እና የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ብሏል።