የደመራ ሥነ – ሥርዓት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተከናወነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደመራ ሥነ – ሥርዓት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሃይማኖታዊ ሥርዓተቶች ተከናውኗል፡፡
በዚሁ መሠረት÷ በሐዋሳ፣ ጅማ፣ ሐረር፣ ደብረ ብርሃን እና ነቀምቴ ከተሞች የደመራ ሥነ – ሥርዓት ተከናውኗል፡፡
በተጨማሪም በባሕር ዳር፣ አዳማ፣ አሶሳ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የሃይማኖት አባቶች፣ ካህናት፣ የእምነቱ ተከታዮች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ጎብኚዎች በተገኙበት ነው ሥነ- ሥርዓቱ ተከናውኗል፡፡
በጥላሁን ይልማ፣ ተሾመ ኃይሉ፣ ተስፋሁን ከበደ፣ አላዩ ገረመው እና ገላና ተስፋ