Fana: At a Speed of Life!

ኳታር የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማይጠቀሙ ሰዎችን 53 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ልትቀጣ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኳታር ዜጎቿ የአፍ መሸፈኛ ጭምብልን በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ወሰነች።

የኳታር የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከፊታችን እሁድ ጀምሮ ከቤት ውጭ የሚንቀሳቀሱ ዜጎች የአፍ መሸፈኛ ጭምብል በግዴታ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ይህን የማያደርጉ ከሆነ ግን 53 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይቀጣሉ ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ።

ከዚህ ባለፈም ሶስት አመት የእስር ቅጣት ሊቀጡ ይችላሉም ነው የተባለው።

አዲሱ ድንጋጌ ግን ብቻውን ሆኖ የሚያሽከረክርና የአፍ መሸፈኛ ጭምብል የማይጠቀም አሽከርካሪን አይመለከትም ተብሏል።

በኳታር 28 ሺህ 272 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ሲያዙ 14 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.