Fana: At a Speed of Life!

ኮቪድ19ን ለመከላከል ንጽህናን መጠበቅ ቀዳሚ መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ ወተር ኤይድ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮቪድ19ን ለመከላከል ውሃን ማቅረብና ንጽህናን መጠበቅ ቀዳሚ መፍትሄ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ ወተር ኤይድ አስታወቀ።

ድርጅቱ እጅን መታጠብ ሰዎችን ከኮቪድ19 ለመከላከል ወሳኝ በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሽታውን ለመግታት ውሃን ማዳረስና ንፅህናን መጠበቅ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት ብሏል።

73ኛው ዓለም አቀፍ የጤና ጉባዔ የፊታችን ሰኞ በዓለም የጤና ድርጅት አባል ሃገራት የጤና ሚኒስትሮች ተሳታፊነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

በአውሮፓ ህብረት ኮቪድ19 መከላከል በሚል የቀረበው ሃሳብ በሽታውን ለመከላከል እጅግ ወሳኝ ስለሆነው የውሃ አቅርቦትና ንጽህና ጉዳይ ምንም ያለው ነገር የለም።

ወተር ኤይድ በሽታውን በመከላከል ረገድ ትልቅ ፋይዳ ባለው የውሃ ጉዳይ በፖለቲካም ይሁን በገንዘብ አቅርቦት ውሳኔዎች ላይ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ትልቅ ትኩረት በመስጠት በጉባዔው ላይ ኮቪድ19ኝን ለመከላከል ውሃና ንጽህና በተለይ ለደሃና መካከለኛ ሃገራት ያለውን ወሳኝ ድርሻ በማውሳት ተገቢው ቦታ እንዲሰጠው ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

በዓለም የጤና ድርጅትና ዓለም አቀፍ የህፃናት ድርጅት ግምት መሰረት 3 ቢሊየን ሰዎች ውሃና ሳሙና እንደማያገኙም ድርጅቱ አስታውቋል።

በተጨማሪም 40 በመቶዎቹ የጤና ተቋማት የእጅ ንፅህና ማከናወን የሚያስችሉ ቁሳቁሶች እንዳልተሟላላቸውና በቤትና ጤና ተቋማት ውሃና ሳሙና ማግኘት በኢትዮጵያ ተመሳሳይ መሆኑንም አውስቷል።

በመሆኑም የዓለም አቀፉ የጤና ጉባዔ መከላከልንና ማዳንን ያካተተ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ ሲነድፍ የውሃና ንጽህናን ወሳኝ ሚና ባካተተ ሁኔታ መፈፀም አለበት ብሏል።

ለኮቪድ19 ክትባት እስከሚገኝለት ድረስ ንጽህናን መጠበቅ ቫይረሱን ለመግታት ለሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችና በሽታው ከፍተኛ ስጋት ለደቀነባቸው ማህበረሰቦች እጅግ ወሳኝ መሆኑንም ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ገልጿል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.