የመስቀል ደመራ እና የመውሊድ በዓላት በሰላም ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ የተከበሩት የመስቀል ደመራ እና የመውሊድ በዓላት በሰላም መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡
ግብረ ኃይሉ ቅደመ ዝግጅት አድርጎ የአዝማሚያ ትንተና በማካሄድ ተጋላጭ ቦታዎችንና አካባቢዎችን ለይቶ የሰው ኃይል በማሠማራቱ፣ ለሥራው አጋዥ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀሙ እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ በመስራቱ በዓላቱ በሰላም መጠናቀቃቸው ተመላክቷል፡፡
በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካለትም የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡
በቀጣይ በሚከበሩ ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ላይም ሕብረተሰቡ እንደተለመደው ቀና ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡