በዓለም በኮሮና ቫይረስ የሟቾች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ ደረሰ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ ደረሰ።
እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ 303 ሺህ 438 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
ከዚህ ውስጥ በአሜሪካ 86 ሺህ 912 ሰዎች፣ በብሪታኒያ 33 ሺህ 614 እንዲሁም በጣሊያን 31 ሺህ 368 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።
በተጨማሪም 4 ሚሊየን 527 ሺህ 811 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
45 ሺህ 560 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና መስጫ ውስጥ እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ነው የተባለው።
ምንጭ፦ www.worldometers.info/