Fana: At a Speed of Life!

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብፁዕ አቡነ ሰላማ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም በሆስፒታል በሕክምና ላይ እንዳሉ ዛሬ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መረጃ ያመላክታል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከአባታቸው ከአቶ ገብረሥላሴ ገ/መድኅንና ከእናታቸው ወይዘሮ ብዙነሽ ወንድሙ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ልዩ ስሙ በዓታ ለማርያም በተባለ ቦታ በ1934 ዓ.ም ነበር የተወለዱት።

ፊደልና ንባብ እና የቃል ትምሕርት በመማር ለግብረ ዲቁና የሚያበቃቸውን ትምሕርት ከየኔታ ክንፈ ገብርኤል በመማር ማዕረገ ዲቁናን ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ተቀብለዋል።
ብፁዕ አቡነ ሰላማ በቀድሞ ስማቸው ሊቀ ሥልጣናት አባ ሐረገ ወይን ገብረ ሥላሴ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት እና መዝገብ ቅዳን ከተለያዩ ሊቃውንት ከተማሩ በኋላ ለመምህርነት በቅተዋል።
በወቅቱ የጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ የቅስናና የቁምስና ማዕረግ ተቀብለዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.