Fana: At a Speed of Life!

6 ሺህ ዓመት እድሜ ያላቸው ጥንታዊ ጫማዎች በስፔን ዋሻ ተገኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6 ሺህ ዓመት እድሜ ያላቸው ጥንታዊ የአውሮፓውያን ጫማዎች ስፔን መገኘታቸውን ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡

ጥንታዊ ጫማዎቹ በደቡባዊ ምዕራብ ስፔን በአንዳሉሺያ ግዛት ‘የሌሊት ወፍ ዋሻ’ ተብሎ በሚጠራው ዋሻ ውስጥ መገኘታቸውን ነው ተመራማሪዎቹ የገለጹት።

ከጫማዎቹ በተጨማሪ ቅርጫት እና ጥንታዊ ሰዎች ይገለገሉባቸው የነበሩ መገልገያዎች፣ ከእንጨት የተሰሩ መሳሪያዎች፣ ከወርቅ የተሰራ ዘውድ እና የተለያየ ቁሳቁስ በዋሻው ውስጥ መገኘታቸውም ነው የተገለፀው፡፡

በዋሻው ውስጥ ዝቅተኛ እርጥበት አዘል አየር እና ቀዝቃዛ ንፋስ መኖሩ ቁሳቁሶቹ እንዲጠበቁ እና ሳበላሹ እንዲቆዩ ማድረግ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

የጥናቱ ተባባሪ ማሪያ ሄሬሮ ኦታል÷ ቁሳቁሶቹ በደቡብ አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ጥንታዊ የእፅዋት ውጤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ቁሳቁሶቹ የተሰሩበት መንገድ እና ተጠብቀው ለብዙ ዓመታት እንዲቆዩ የተደረገበት ጥበብ ጥንታዊ ሰዎች የቴክኖሎጂ ክህሎት እንደነበራቸው የሚያሳይ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ጥንታዊ ሰዎች ጫማዎችን ለመስራት የተለያዩ የሳር አይነቶችን እና ቆዳ እንዲሁም ሎሚን ይጠቀሙ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ጫማዎቹ በ2008 በአርሜኒያ ዋሻ ውስጥ ከተገኙት እና ከ5 ሺህ 500 ዓመታት በላይ እድሜ እንዳላቸው ከተገለፁት ጫማዎች የበለጠ እድሜ አላቸው መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.