ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) የሞያሌ ድንበር ተሻጋሪ ልማት አመቻች ጽህፈት ቤትን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸኃፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር ) የሞያሌ ድንበር ተሻጋሪ ልማት አመቻች ጽህፈት ቤትን መርቀው ከፍተዋል፡፡
ወርቅነህ(ዶ/ር) ጽህፈት ቤቱን መርቀው የከፈቱት ከማርሳቢት ግዛት ርዕሰ መስተዳድር መሀሙድ አሊ ጋር በመሆን ነው፡፡
ጽህፈት ቤቱ በሞያሌ – ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የሚገኙ ማህበረሰቦችን ይደግፋል መባሉን ከኢጋድ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።