Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ በተፈጸመ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን በአጥፍቶ ጠፊ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡

ጥቃቱ በፓኪስታን ደቡብ ምዕራብ ባሎቺስታን ማስቱንግ ከተማ በሚገኝ አንድ መስጅድ አጠገብ መፈጸሙን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የቦምብ ጥቃቱ የነቢዩ መሐመድ ልደት በዓልን ለማክበር በአካባቢው በሚገኝ መስጅድ በተሰበሰቡ ምዕመናን ላይ መፈጸሙ ተጠቁሟል፡፡

በአጥፍቶ ጠፊው በተፈጸመው ጥቃትም እስካሁን ከ50 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ነው የተገለጸው፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ በአሥራዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን÷ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.