Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ቻይና የትብብር ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ደረጃውን የጠበቀ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰራር ለመዘርጋት ዕቅድ እንዳለው የኢትዮ ቻይና የትብብር ኮሚቴ ገለጸ፡፡

በኢትዮ ቻይና የትብብር ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቤቲ ዙ (ዶ/ር) የተመራ የልዑክ ቡድን ከምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

ኮሚቴው በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ደረጃውን የጠበቀ የአገልግሎት አሰራር ለመዘርጋት ዕቅድ እንዳለው መግለጹን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ይሄም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጎልበት እንዲሁም በኢትዮጵያ የቻይና ኩባንያዎችን እና ባለሃብቶችን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚረዳ ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮሚቴው በገጠር አካባቢ ተሰማርተው እየሰሩ ላሉ የቻይና የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የፀሐይ ሀይልን በመጠቀም የኤሌትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል ፕሮጀክት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

በዚሁ ወቅት ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን÷ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ኮሚሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.