ቢዝነስ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

By Tamrat Bishaw

September 29, 2023

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ በዚሁ መሠረት 1. ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም 2. ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም 3. ነጭ ጋዝ በሊትር 76 ብር ከ75 ሳንቲም 4. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 70 ብር ከ83 ሳንቲም 5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም 6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ83 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡