Fana: At a Speed of Life!

በሜዲትራኒያን ባሕር የሚሞቱ ስደተኞች ቁጥር በ3 እጥፍ ጨመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሉ በሜዲትራኒያን ባሕር የሚሞቱ አፍሪካውያን ስደተኞች ቁጥር በሦስት እጥፍ መጨመሩን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ለአብነትም ካለፈው ሰኔ ወር እስከ ነሐሴ ድረስ 990 አፍሪካውያን ስደተኞች በሜዲትራኒያን ባሕር ሕይወታቸው ማለፉን የድርጅቱ ሪፖርት አመላክቷል፡፡

ባለፈው ዓመት ሕይወታቸው ያለፈ አፍሪካውያን ስደተኞች ቁጥር 334 እንደነበር አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በአውሮፓ ጥገኘትን ፍለጋ በጉዞ ላይ የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የገለጸው ድርጅቱ÷ በጉዳዩ ላይ የፖለቲካ ቁርጠኝነት አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰው ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.