አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኙ
ሰራዊቱ ተስፋው የሞላ እና ለራሡም ሆነ ለቤተሰቡ የነገ ህይወት እንዳያስብ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የጀመረውን የጎላ ሚና አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ገልፀዋል።
“ሰራዊታችን በምግብም ሆነ በአልባሳት ሌላ አምራች ሀይል ሳያስፈልገው እራሱን እንዲችል የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የጀመረው ተግባር የሚደነቅ ነው” ብለዋል።
የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው የፋውንዴሽኑን ገቢ በራስ አቅም ማሳደግና የሠራዊቱን ኑሮ መደገፍ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።
ወደፊትም ፋውንዴሽኑ በማዕድን፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በከተማ ልማት ላይ በማተኮር የሠራዊቱን ኑሮ የሚያሻሽል ተቋም ሆኖ መቀጠል እንደሚኖርበትም አስገንዝበዋል።