Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ከተማ በእሳት አደጋ ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች የተገነቡ የንግድ ቤቶች ተሰጡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማእከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች የተገነቡ 336 ጊዜያዊ የንግድ ቤቶች ለነጋዴዎች ተሰጥተዋል።
በሶማሌ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀሊሞ ሀሰን እና የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዚያድ አብዲ (ኢ/ር) ሰብሳቢነት የተወቀረው የተጎጂዎች ሀብት አሰባሳቢና መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ በእሳት አደጋው ንብረታቸውን ላጡ ነጋዴዎች የተገነቡ የንግድ ቤቶችን አስተላልፏል።
ከ100 ሺህ ብር ያነሰ ሀብት ለወደመባቸው ነጋዴዎች 100 በመቶ ፣ ከ100 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር ሀብት ለተጎዳባቸው ነጋዴዎች 50 በመቶ ፣ ከ500 ሺህ እስከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ለወደመባቸው ነጋዴዎች ደግሞ 40 ከመቶ ክፍያ መሰጠቱም ተመላክቷል፡፡
እንዲሁም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን እስከ 3 ሚሊየን ብር ለወደመባቸው 20 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሆነ ንብረት ላጡ ነጋዴዎች ደግሞ ስራ ለመጀመር የሚያስችላቸውን 10 በመቶ ክፍያ እንደተሰጣቸው ኮሚቴው ማስታወቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.