የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገለጸ

By Amele Demsew

October 01, 2023

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን ቅዳሜ ለሚከበረው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል።

የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር እየተደረገ ያለውን ዝግጅት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም ለበዓሉ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ-ዝግጅት ተግባራት በጥሩ መልኩ እየተጠናቀቁ እንደሚገኙ መገለጹን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

እስከ በዓሉ መዳረሻ ባሉ ቀሪ ቀናት ውስጥ የተጀመሩ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡም ተጠቁሟል፡፡