Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ ወታደሮቿን ለዩክሬን የመላክ ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን የመላክ ፍላጎት እንዳላት የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ በዩክሬን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትሩ በዩክሬን ቆይታቸውም ÷ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በውይይታቸውም የዩክሬን ወታደሮችን የሥልጠና መርሐ ግብር ማስፋፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም የብሪታንያ ባህር ኃይል ጥቁር ባህርን በመከላከል ዩክሬንን መደገፍ በሚችልበት አግባብ ላይ በትኩረት መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ግራንት ሻፕስ በዩክሬን ጉብኝታቸው ÷ ሁለቱ ሀገራት በጋራ የሚሰሩባቸው ሰፊ እድሎች እንዳሉ መገንዘባቸውን ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም ብሪታንያ በዩክሬን የተለያዩ ጦር መሳሪያዎችን ማምረት የምትችልበት ምቹ ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡

ሚኒስትሩ ብሪታንያ ዩክሬንን ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ሀገሪቱ የመላክ ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውም ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.