በፕሪሚየር ሊጉ ጅማሮ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም ዛሬ ተጀምሯል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9፡00 ላይ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና ጋር 12፡00 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ ነው የተጀመረው፡፡
በመርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ያሸነፈ ሲሆን÷ ኤርሚያስ ሹምበዛ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል፡፡
እንዲሁም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡