Fana: At a Speed of Life!

ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ምኅዳር ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሠራር ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሰው ኃይል ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ ምቹ  ምኅዳር ለመፍጠር የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የልማት አጋሮች እና የሲቪል ማኅበራትን ንቁ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

2ኛው የአፍሪካ የሰው ሃብት ልማት ጉባዔ “ራስን የሚደግፍ ሥነ-ምኅዳር መገንባት፤ የቀጣይ ሥራ የሚፈልገው ክኅሎት፣ የክኅሎት ልማት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለሰው ሃብት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የሥራ ገበያው የሚፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትም የቴክኒክና ሙያ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከክኅሎት ልማቱ በተጨማሪ የተግባር ልምምድ እና የሥራ ላይ ስልጠና ወሳኝ ስትራቴጂ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባም ነው ያመላከቱት፡፡

እንደ ሀገር እየተደረገ ያለው ጥረት የተቀናጀ፣ ራሱን የቻለ እና ፍላጎት መር ክኅሎት፣ የሥራ ዕድል እና ለሥራ ምቹ የሆነ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር መሆኑን ገልጸው÷ ይህም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የልማት አጋሮች እና የሲቪል ማሕበረሰብን ንቁ ተሳትፎ  እንደሚጠይቅ አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.