Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ያለፉት ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል የ2016 በጀት ዓመት ያለፉት ሶስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት እየተገመገመ ነው፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ ÷ የግምገማ መድረኩ የክልሉን ያለፉት ሶስት ወራት የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም ድክመትና ጥንካሬ መለየት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለተስተዋሉ ተግዳሮቶች ፈጣን ምላሽ በመስጠት የዜጎችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ፣ የክልሉ ካቢኔ እና የዞን አስተዳዳሪዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኑኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.