በምዕራብ ጉጂ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪም 8 ሺህ 929 አባዎራዎች እና 63 ሺህ ቤተሰቦች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ነው የተባለው።
እንዲሁም በወረዳው በሚገኙ 17ቀበሌዎች 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
እንደ ዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት መረጃ በጎርፍ አደጋው ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ፣ የአልባሳት እና የተለያዩ እርዳታዎች እየተደረገላቸው ይገኛል።